አማርኛ Group እና Team – ቡድን የሚል ተመሳሳይ ፍቺ ያስቀምጥላቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁለት ቃላቶች ልዩነታቸው ሰፊ ነው፡፡ Group ስብስብን የሚገልጽ ሲሆን Team ውህደትና ቅንጅትን ሲያሳይ በጋራ አብሮ የመስራትና ከፍ ያለ ውጤትና ዕሴት የመፍጠርን ፍልስፍና ያካትታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ Team የሚለው ቃል ዕጅግ የላላ ትርጉም ተሰጥቶት Group የሚለውን ቃል በሚገልጽ መልኩ አብረው የሚሰሩ የሰዎችን ስብስብ ለመግለጽ ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ይህ ፍጹም ስህተት ነው፡፡ ለምሳሌ የአመራር ቲም (Leadership Team) ወይንም የበላይ ቲም (Senior Management Team) የሚሉ አገላለጾች አባላቱ ፍጹም በቲም የመስራት ዝንባሌ በማይታይባቸው ሁኔታዎች ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ቲም ከቡድን በበርካታ መስፈርቶች በዕጅጉ የተለየ ነው፡፡ ሰዎች በGroup ሲሰሩ ግላዊ ውጤታቸው ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን Team ግን ለጋራ ውጤት በጋራ ተጠያቂነት ላይ ያተኩራል (እዚህ ላይ የሩጫና የእግር ኳስ ስፖርቶችን እንደምሳሌ መውሰድ ይቻላል)፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግም የሚከተሉት ጎልተው የሚወጡ ልዩነቶች ናቸው፡፡ • ትብብርና ቅንጅት የሚጠይቅ የጋራ ዓላማ • በሚሰሩት ስራ የሚኖራቸው መተሳሰር፤ ለምሳሌ የአንዱ ስራ በሌላኛው ላይ የተመሰረተ መሆን • እርስ በርስ ባላቸው የጋራ መደጋገፍ • ለጋራ ጥረታቸውና ድክመታቸው በጋራ የሚወስዱት ኃላፊነት ናቸው፡፡